የደደቢቱ አሰልጣን ዮሃንስ ሳህሌ ስማቸው ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቅጥር ጋር ተያይዞ መነሳቱን አስተባበሉ፡፡
አሰልጣኙ ቡድናቸው ኢትዮጵያ ቡናን ካሸነፈበት የፕሪሚር ሊግ ጨዋታ በኋላ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ስለ አሰልጣኝ ቅጥሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
‹‹ ስለ ብሄራዊ ቡድኑ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ለአሰልጣኝነት ለመወዳደር ያስገባሁት ምንም አይነት ፋይልም የለም፡፡ ከፌዴረሽኑ ጋርም በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ውይይት አላካሄድኩም፡፡ ስለዚህ ምንም በማላውቀው ጉዳይ ላይ ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አልፈለክግም፡፡ ›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡