#CAFCL : የሳላዲኑ አል-አሃሊ ምድብ ውስጥ ሳይገባ ቀረ፤ የአበባው አል-ሂላል ዛሬ ይጫወታል

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የግብፁ አል አሃሊ በሞሮኮው መግርብ ቱቶዎን በመለያ ምት 4ለ2 ተሸነፎ ወደ ምድብ ሳይገባ ቀርቷል፡፡ አሰልጣኝ ሁዋን ካርሎስ ጋሪዶ ኢትዮጵያዊውን ሳላዲን ሰዒድን በተጠባባቂ ወንበር ላይ አስቀምጠው ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡ ጨዋታውን አል አሃሊ በአብደላ ኤል-ሳዒድ ግብ 1ለ0 ቢያሸነፍም በመለያ ምት የሞሮኮው ክለብ አሸንፎ ወደ ምድብ አልፏል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ሞሮካ ላይ በመጀመሪያው ዙር ተጫውተው መግርብ ቱቶዎን ለለ0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

የሱዳኑ ክለብ አል-ሂላል ዛሬ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ክለብ የሆነው ሳንጋ ባሌንዴን ኦምዱሩማን ላይ ይገጥማል፡፡ ኢትዮጵያዊው ግራ ተመላላሽ አበባው ቡጣቆ በጨዋታው ላይ የመሰለፍ ዕድል ሊያገኘ ይችላል፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ ኮንጎ ላይ ሂላል ሳንጋ ባሌንዴን በተከላካዩ ሳይፍ ማሳዊ ግብ 1ለ0 አሸንፏል፡፡ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ሂላል ምድብ ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡ አበባው ቡጣቆም የመጀመሪያው በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ የሚጫወት ኢትዮጵያዊ የሚሆንበት ዕድል ይፈጠራል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *