ኡመድ ኡኩሪ ዳግም ወደ ኢቲሃድ አሌክሳንደሪያ…?

ኢትዮጵያዊው አጥቂ ኡመድ ኡኩሪ ከኢቲሃድ አሌክሳንደሪያ ጋር ለመቀጠል መስማማቱን ከግብፅ የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ኡመድ ከአሌክሳንደሪያው ክለብ ጋር ባለመስማማት ክለቡን ለቆ ከቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ሁለቱ አካላት ያልተስማሙበት ምክንያት ደግሞ በደሞዝ አከፋፈል ጉዳይ ነበር፡፡

እስከባለፈው ሰኞ ድረስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ልምምድ የሰራው ኡመድ ከሰኞ በኃላ ወደ ግብፅ ማቅናቱ ታውቋል፡፡ ከግብፅ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ኢቲሃድ አሌክሳንደሪያ እና ኡመድ ስምምነት ላይ መድረስ ችለዋል፡፡ ኡመድ ከቀጣዩ የውድድር ዘመን ጀምሮ ለኢቲሃድ አሌክሳንደሪያ እንደሚጫወት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሶከር ኢትዮጵያ ያነጋገረቻቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ አሽኔ “ስለጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ኡመድ እስከ ሰኞ ድረስ አብሮን ልምምድ ሰርቷል፡፡ ባሳለፍነው ጥር ልናስፈርመው ሞክረን ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ይህም የሆነው ኢቲሃድ አሌክሳንደሪያ ጋር ቀሪ የውል ስምምነት ስለነበረው ነው፡፡” ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *