በኅይሉ አሰፋ በአልጄሪው ኤም.ሲ. ኤል ኡልማ ተፈልጓል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የመስመር ተጫዋች የሆነው በኅይሉ አሰፋ በአልጄሪያው ኤም.ሲ. ኤል ኡልማ መፈለጉን ፕላኔት ስፓርት ዘግቧል፡፡ በኅይሉ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ውል በመጪው የክረምት ወር የሚጠናቀቅ ሲሆን ወደ አልጄሪያው ክለብ ለሙከራ ሊሄድ እንደሚችል ዘገባው አመላክቷል፡፡ በኅይሉ በኤም.ሲ. ኤል ኡልማ ዓይን ውስጥ ሊገባ የቻለው ባሳለፍነው የካቲት ወር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኤም.ሲ. ኤል ኡልማ ጋር ባደረገው የካፍ ቻምፒንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር ጨዋታ ባህር ዳር ላይ ቱሳ ኡልማ ላይ ከርቀት ግሩም ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *