የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ባለፈው እሁድ በአዳማ ከነማ 4-2 በተሸነፉበት ጨዋታ ከፍተኛ የዳኝነት በደል እንደደረሰባቸውና ለፌዴሬሽኑ ክስ እንዳስገቡ ተናግረዋል፡፡
አሰልጣኝ ፀጋዬ በአዳማው ጨዋታ የዳኝነት ውሳኔዎች ለሽንፈታቸው ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል ‹‹ በጨዋታው የፍፁም ቅጣት ምት አላግባብ ተሰጥቶብናል፡፡ አዳማዎች ካስቆጠሯቸው ግቦች አንዷ የተቆጠረችው ከጨዋታ ውጪ በሆነ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ የጨዋታውን ውጤት ለመቀበል ያስቸግረኛል፡፡ ›› ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል፡፡
አሰልጣኙ አያይዘውም ለፌዴሬሽኑ ክስ እንዳስገቡ እና ነገ ውሳኔ እንደሚብቁ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በቪድዮ የተደገፈ ማሰረጃ አቅርበናል፡፡ ነገ ውሳኔ እንደሚሰጡን ተስፋ አደርጋለሁ ›› ብለዋል፡፡