በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ጎንደር ተጉዞ በድል ተመልሷል፡፡
ዳሽን ቢራዎች ቶጓዊው አጥቂ ኤዶም ሆሶሮቪ ባስቆጠረው ግብ የመጀመርያውን አጋማሽ በ1-0 መሪነት ቢጨርሱም በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው አዳነ ግርማ አከታትሎ ባስቆጠራቸው ግቦች 2-1 አሸንፎ ከደደቢት ጋር ያለውን የ8 ነጥብ ልዩነት ልዩነት ማስጠበቅ ችሏል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ በ48 ነጥቦ0ች ሊጉን እየመራ ሲሆን ተከታዩ ደደቢት ተስተካካይ ጨዋታውን በሽንፈት ካጠናቀቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ አንድ ተከታዩን ጨዋታ ማሸነፍ በቂው ነው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአሰልጣኝ ስንብት እና ከውድድር ዘመኑ ውጣ ውረዶች በኋላ ለአመታት ያሸነፈውን ዋንጫ በድጋሚ ሊያነሳ ተቃርቧል፡፡