በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልድያ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ሲያረጋግጥ ሙገር ሲሚንቶም የወልድያን እግር ሊከተል ተቃርቧል፡፡
መልካ ቆሌ ላይ አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደው ወልድያ 1-0 ተሸንፏል፡፡ ሽንፈቱን ተከትሎም 3 ጨዋታ እየቀረው 12ኛ ደረጃ ላይ ካለው ኤሌክትሪክ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 12 በመድረሱ ባለፈው አመት ወደነበረበት ብሄራዊ ሊግ መውረዱን አረጋግጧል፡፡
አሰላ ላይ አዳማ ከነማን ያስተናገደው ሙገር ሲሚንቶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ ከኤሌክትሪክ ጋር የነበረውን ልዩነት የማጥበብ እድሉን አበላሽቷል፡፡ ሙገር 12ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ኤሌክትሪክ ጋር ያለው የነጥ ልዩነት 4 ሆኗል፡፡
ይርጋለም ላይ መከላከያን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና 0-0 አቻ ተለያይቶ ለዋንጫ የነበረው ተስፋ አክትሟል፡፡ ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ሶስቱንም ጨዋታ አሸንፎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስቱንም ጨዋታ መሸነፍ ይኖርበታል፡፡
አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ወላይታ ድቻን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በአንዋር ያሲን እየተመራ የመጀመርያ ነጥቡን ሲያገኝ ከ5 ተከታታይ ጨዋታ ሽንፈት በኋላ ያገኘው የመጀመርያ ነጥብ ሆኗል፡፡
የ23ኛ ሳምንት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው
ኤሌክትሪክ 0-4 ደደቢት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-1 ሀዋሳ ከነማ
ዳሽን ቢራ 1-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሲዳ ቡና 0-0 መከላከያ
ሙገር ሲሚንቶ 1-1 አዳማ ከነማ
ወልድያ 0-1 አርባምንጭ ከነማ
ኢትዮጵያ ቡና 0-0 ወላይታ ድቻ