ፕሪሚር ሊግ ፡ ሀዋሳ ከነማ በሊጉ መቆየቱን አረጋገጠ

 

ዛሬ በተካሄደ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ሀዋሳ ከነማ ደደቢትን አሸንፎ በፕሪሚር ሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል፡፡

የሀዋሳ ከነማዎችን ጎሎች ተመስገን ተክሌ በ30 እና 46ኛው ደቂቃ ያስቆጠረ ሲሆን በዘነምድሮ ፕሪሚር ሊግ ያስቆጠራቸውን ግቦች ቁጥርም 9 አድርሷል፡፡ የደደቢትን ብቸኛ ግብ ከመረብ ያሳረፈው ጋናዊው ጋብሬል አህመድ በ41ኛው ደቂቃ ነው፡፡

ረጅም ኮሶችን በተደጋጋሚ በ ሁለቱም ቡድኖች በኩል በተመለከትንበት የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ጎል በመድረስ በኩል የቀዘቀዙ ቢሆኑም የጨዋታዋቹ ሶስቱም ጎሎች በዚው በ የመጀመሪያ አጋማሽ ነበር የተቆጠሩት፡፡ ተመስገን ተክሌ ምርጥ ሆኖ ባመሸበት ጨዋታ ሀዋሳ ከነማዎች በ30 ነጥብ ከሊጉ የመውረድ ስጋታቸውን ለ ኤሌክትሪክና ለሙገር ትተው ለ2008 የኢትዮጺያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን እቅዳቸውን ማስቀመጥ ጀምረዋል፡፡

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የሀዋሳ ከነማው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ግዴታቸውን እንደተወጡ ተናግረዋል፡፡ “ግዴታችንን የተወጣንበት ጨዋታ ነበር፡፡ እኔ ከመምጣቴ በፊት ቡድኑ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ነበር፡፡ እኔ ከመጣው በሑዋላ ያደረኩት ልጆቹን ማነሳሳት ብቻ ነው፡፡”

“በትንንሽ ቡድኖች የጣልናቸው ነጥቦች ናቸው እንጂ ከዚህ በፊትም አለመውረዳችንን ማረጋገጥ እንችል ነበር›› ሲል ነው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አሳቡን የገለፀው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *