አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ቴክኒክ ዳይሬክተር ሾሟል

በቅርቡ ከአሰልጣኝ ከእስማኤል አቡበከር ጋር የተለያየው አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ቴክኒክ ዳሬክተር መሾሙ ታውቋል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው አዲስ አዳጊው አዲስ አበባ ከተማ የቡድኑን አቅም ለማሳደግ በማሰብ አቶ ፍስሐ አገኘውን ቴክኒክ ዳይሬክተር አድርጎ መቅጠሩ ተረጋግጧል። አቶ ፍስሀ ከዚህ ቀደም በፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት የሰሩ ሲሆን ከዚሁ ባሻገር በኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ፋሲል ከነማ እና በቅርቡ ወደ ንግድ ባንክ የዞረው ኢኮሥኮ በሥራ አስኪያጅነት የሰሩ ልምድ ያላቸው ባለሙያ ናቸው።

በሌላ ዜና በአሰልጣኝ እስማኤል አበቡበከር ምትክ ሌላ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም የክለቡ አመራሮች የተለያዩ አማራጮችን ለመጠቀም እያጤኑ እንደሆነ ሰምተናል።