ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ተካፋዩ ሻሸመኔ ከተማ አሰልጣኝ ኤፍሬም ዓለምነህን በዋና አሰልጣኝነት ሲሾም ረዳቱንም አሳውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ባለፈው የውድድር ዓመት በ25 ነጥቦች ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቆ የነበረው ሻሸመኔ ከተማ ለዘንድሮው የ2014 የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት በማሰብ በተጫዋችነት ረዘም ያለ ልምድ ያለውን ኤፍሬም ዓለምነህን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሯል፡፡ የእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኑን በትወልድ ከተማው ሻሸመኔ ከጀመረ በኋላ በሀረር ቢራ ፣ መድን ፣ መከላከያ ፣ ደቡብ ፓሊስ በድምሩ ሰባት ክለቦች ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈው ኤፍሬሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥም ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ባለፈው ዓመት የሻሸመኔ የአሰልጣኝ ቡድን አባል ነበር። ዘንድሮ ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት ክለቡን ተረክቧል፡፡

ከዋና አሰልጣኙ በተጨማሪ ክለቡ በተለያዩየ የዕድሜ ዕርከኖች ውስጥ ሲያሰለጥን የነበረውን ትቤሶ ደስታን በረዳትነት፣ የቀድሞው አንጋፋ ግብ ጠባቂ አጥናፉ ታደሰን ውል ደግሞ በማራዘም በክለቡ መቀመጫ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡