ዚምባብዌን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከዚምባቡዌ ጋር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍን ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

ኳታር ለምታስተናግደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሰባት ከጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የተደለደሉት ዚምባቡዌ እና ኢትዮጵያ ገና በጊዜ ከምድባቸው መውደቃቸውን ማረጋገጣቸው ይታወሳል። ምንም እንኳን ቡድኖቹ ዋና አላማቸውን ባያሳኩም የመርሐ-ግብር ማሟያ የሆኑ ጨዋታዎች ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን ዛሬ ከሰዓትም የምድኑ የመጨረሻ ደረጃን ይዞ ላለማጠናቀቅ እና ለክብር ብለው የመጨረሻ ጨዋታቸውን ሀራሪ ላይ ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከጋና ጋር በጥሩ እንቅስቃሴ ተጫውተው ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታም ዛሬ ሁለት ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ ለመግባት ተዘጋጅተዋል። በዚህም አስቻለው ታመነ በአህመድ ረሺድ እንዲሁም መስዑድ መሐመድ በሀይደር ሸረፋ ተለውጠዋል።

ግብ ጠባቂ

ተክለማርያም ሻንቆ

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ
አህመድ ረሺድ
ምኞት ደበበ
ረመዳን የሱፍ

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ
ሀይደር ሸረፋ
ሽመልስ በቀለ

አጥቂዎች

አቡበከር ናስር
ጌታነህ ከበደ
ዳዋ ሁቴሳ