አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ሲዳማ ቡና ከ ሰበታ ከተማ

የአራተኛ ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታን የተመለከቱ አሁናዊ መረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

በሦስተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር በሀዋሳ ከተማ የተረቱት ሲዳማ ቡናዎች ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ጨዋታ ተስፋዬ በቀለን በጊት ጋትኩት፣ ብርሃኑ አሻሞ በሙሉዓለም መስፍን፣ ብሩክ ሙሉጌታ በዳዊት ተፈራ እንዲሁም ፍራንሲስ ካሀታ በሀብታሙ ገዛኸኝ ለውጠው ጨዋታውን ቀርበዋል።

ተጋባዦቹ ሰበታ ከተማዎች ደግሞ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ነጥብ ከተጋሩበት ፍልሚያ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ወልደአማኑኤል ጌቱ በቢያድግልኝ ኤሊያስ፣ ክሪዚስቶም ንታንቢ በዮናስ አቡሌ እንዲሁም ዱሬሳ ሹቢሳ በዘላለም ኢሳይያስ ተለውጠዋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የዕረፍት ጊዜው ከሽንፈት መልስ የተገኘ መሆኑ ራሳቸውን ለማየት እንደጠቀማቸው ሲናገሩ ዛሬ ጨዋታውን ለማሸነፍ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ አላስፈላጊ ጫና ውስጥ ላለመግባት ማሸነፍን አስበው እንደሚገቡ የገለፁት አሰልጣኝ ስዘላለም ሽፈራው የዕረፍት ጊዜው ስህተቶችን ለማረም ቢጠቅማቸውም ከተጫዋቾች ጉዳት አንፃር ደግሞ አመርቂ እንዳልነበር ገልፀዋል።

ይህንን ጨዋታ ፌዴራል ዋና ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ በአልቢትርነት የሚመሩት ይሆናል።

ቡድኖቹ በመጀመሪያ አሰላለፍ የሚጠቀሟቸው ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው።

ሲዳማ ቡና

1 ተክለማርያም ሻንቆ
24 ጊት ጋትኩት
3 አማኑኤል እንዳለ
5 ያኩቡ መሐመድ
21 ሰለሞን ሀብቴ
10 ዳዊት ተፈራ
20 ሙሉአለም መስፍን
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
7 ፍሬው ሰለሞን
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
11 ይገዙ ቦጋለ

ሰበታ ከተማ

30 ለዓለም ብርሀኑ
13 ታፈሰ ሰርካ
15 በረከት ሳሙኤል
12 ቢያድግልኝ ኤሊያስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
21 በሃይሉ ግርማ
19 ዮናስ አቡሌ
22 ዘላለም ኢሳይያስ
9 ሳሙኤል ሳሊሶ
10 ዘካሪያስ ፍቅሬ
20 ጁኒያስ ናንጄቤ