የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልቂጤ ከተማ 0-0 አርባምንጭ ከተማ

ከአመሻሹ ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሰጡት አስተያየት።

ጳውሎስ ጌታቸው – ወልቂጤ ከተማ

አስተዳደራዊ ጉዳዮች ሜዳ ላይ ስለፈጠሩት ጫና

“ይሄ የተመለከታችሁት ነው በዚህ ላይ መናገር አያስፈልግም የአሰልጣኝ ስራ ያሉትን ተጫዋቾች ይዞ ሜዳ መግባት ነው ይህን አድርጊያለሁ።ስድስት እና ሰባት ቆሚ ተጫዋቾች ሳይኖሩ ተጫዋቾች በተደበላላቀ ሚና ተጫውተው አንድ ነጥብ ማግኘታችን ስኬት ነው።”

ከተጫዋቾቹ የሚፈልገውን ስለማግኘቱ

“ብዙ ተጫዋቾች አሸጋሽገን ነው የተጠቀምነው ያለ መሀል ተከላካይ ነበር ጨዋታውን ያደረጉት በዛሬው ጨዋታ ስለቡድኔ ማውራት ይከብዳል እንደአጠቃላይ ተጫዋቾቼ የሰጣኋቸውን ነገር በአስደናቂ ተጋድሎ ተወጥተዋል።በሙከራ የተሻልን ነበርን በዛሬው ጨዋታ በተጫዋቾቼ ተጋድሎ ደስተኛ ነኝ።”

መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ

ስለኤሪክ ካፓዬቶ ቅያሬ

“የእኛ ቡድን ይታወቃል ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ የሚጫወት ነው ይህንን ግን በመጀመሪያ አጋማሽ ይህን ማድረግ አልቻልንም በሁለተኛው አጋማሽ ግን በጣም የተሻለ ነበር ከዚህ ጋር በተያያዘ ኤሪክ ከተነሳሽነት ጋር በተያያዘ የምንፈልገውን ነገር ማግኘት ስላልቻልን አስወጥተነዋል።በቅያሪው የተሻለ ዕድል እና ጫና መፍጠር ችለናል።”

ሦስት ነጥብ ለማሳካት ስለነበራቸው ፍላጎት

“ከመሪዎቹ ያለንን ልዩነት ለማጥበብ ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን ያንን ለማድረግ ደግሞ በየጨዋታው ሶስት ነጥቦችን ማግኘት ያስፈልጋል ለዚህም በሁለተኛው አጋማሽ ከፍተኛ ጥረት አድርገናል።”

በሁለተኛው አጋማሽ የተሻሉ ስለመሆናቸው

“በመጀመሪያው አጋማሽ በእኛ የግራ መስመር በኩል ተደጋጋሚ የመልሶ ማጥቃት ኳሶችን ይመጡ ነበር ይህን በሁለተኛው አጋማሽ ተነጋግረን ለማቆሞ ሞክረናል በተጨማሪም በሁለተኛው አጋማሽ የእነሱ የመሀል ተከላካይ መውጣቱን ተከትሎ ተደጋጋሚ ያንን ቦታ ታሳቢ ያደረጉ ኳሶችን ለመጫወት ሞክረናል።የጨዋታው ውጤቱ ግን እንደተጠበቅነው አይደለም።”