የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ በቀጣዩ ወር ይደረጋል

በኅዳር ወር መጨረሻ ይደረጋል ተብሎ የተራዘመው የፌዴሬሽኑ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በታኅሣሥ ወር ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ እግር ኴስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ከኅዳር 25 እና 26 ለሁለት ቀናት በአርባ ምንጭ ከተማ ሊያካሄድ የነበረው 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙንና በቀጣይ ወደፊት የሚካሄድበትን ጊዜ እንደሚገልጽ ማሳወቁ ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤው ስለመራዘሙ እንጂ የተራዘመበትን ምክንያት ይፋ ከማድረግ የተቆጠበ ሲሆን መቼ እንደሚደረግ አልተገለፀም ነበር። አሁን ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሠረት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛው በአርባምንጭ ከተማ ታኅሣሥ 23 እና 24 እንደሚደረግ አውቀናል።

ከመደበኛው ጠቅላላ ጉባኤ ባሻገር በዚሁ ዓመት ሰኔ ወር ላይ ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩ ፕሬዝደንት እና ሥራ አስፈፃሚ አካላት ምርጫ እንደሚካሄድ ይታወቃል።