ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላለፈበት

ሲዳማ ቡና በፋሲል ከነማ በተረታበት ጨዋታ በታየው የዲሲፕሊን ግድፈት ዙሪያ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል፡፡

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተደረገው ትላንት ዕለተ ዕሁድ መገባደዳቸው ይታወሳል፡፡ በሳምንቱ በታዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ዙሪያ የሊግ ካምፓኒው የውድድር እና ስነ ስርዓት በታዩ የዲሲፕሊን ዙሪያ ግድፈቶች ዙሪያ ቅጣት ተላልፈዋል፡፡

በዚህም መሠረት ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች የክለቡን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እና የአሰልጣኝ ቡድኑን አባላት፣ የዕለቱን የጨዋታ አመራሮች (ዳኞች) በተደጋጋሚ አፀያፊ ስድብ በመስደባቸው የክለቡ አስተባባሪዎች በበኩላቸው የክለቡ ተጫዋቾች ጨዋታቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከተጫዋቾችና ከቡድን አመራሮች ጋር ግጭት ስለመፍጠራቸው ፣ የስታድየሙ ንብረት የሆኑትን ወንበሮች ስለመነቃቀላቸውና መስታወት በድንጋይ ስለመስበራቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል፡፡

በዚህም መነሻነት የውድድር እና ስነ ስርአት ኮሚቴ ክለቡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጥፋት ሰርቶ መቀጣቱን በመግለፅ ክለቡ በያዝነው የጨዋታ ሳምንት በፈፀመው የዲሲፕሊን ግድፈት የአንድ መቶ ሃምሳ ሺህ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል እና ቡድኑም የሚያደርጋችውን ጨዋታዎች ባለሜዳ ሆኖ ሲጫወት (ከወላይታ ዲቻ እና ከባህርዳር ከተማ) በዝግ ስታድየም እንዲሁም ከሜዳው ውጭ (ከመከላከያ) ሲጫወት ካለ ደጋፊ እንዲጫወት በተጨማሪም የተነቃቀሉ እና የተሰበሩ ንብረቶችን እንዲያሰራ ወይም ባለንብረቱ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስልቶ በሚያቀርበውን ዋጋ መሰረት ክፍያ እንዲፈፀም ተወስኗል ።