የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

ከሰዓታት በኋላ የቦትስዋና አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ ይገኛል። በሁለተኛ ዙር የማጣሪያ መርሐ-ግብር የሩዋንዳ አቻውን ረቶ በሦስተኛ ዙር ከቦትስዋና ጋር የተመደበው ቡድኑም ከሁለት ሳምንታት በፊት ከሜዳው ውጪ ተጉዞ የ3-1 የድል ውጤት ይዞ መመለሱ አይዘነጋም። የመልሱን ጨዋታም ከሰዓታት በኋላ (10 ሰዓት) በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ባደረገው መሠረትም አሠልጣኝ ፍሬው ቦትስዋና ላይ የነበረውን የመጀመሪያ አሰላለፍ ምንም ሳይቀይሩ ጨዋታውን የሚቀርቡ ይሆናል። አሰላለፉም የሚከተለው ነው።

ግብ ጠባቂ

22 እየሩሳሌም ሎራቶ

ተከላካዮች

5 ናርዶስ ጌትነት
6 ብርቄ አማረ
4 ቤተልሔም በቀለ
20 ብዙዓየሁ ታደሰ

አማካዮች

2 ኝቦኝ የን
10 ገነት ኃይሉ
17 መሳይ ተመስገን

አጥቂዎች

13 ቱሪስት ለማ
8 ረድኤት አስረሳኸኝ
14 አርየት ኦዶንግ