አሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ጅማ አባ ጅፋር

ከአስራ ሦስት ደቂቃ በመብራት መቋረጥ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞቹ ለስፖር ስፖርት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ጨዋታው በጠበቃችሁት መልኩ ሄዷል ?

አዎ ውጥረት ያለበት እና ከባድ ጨዋታ ነበር። ይህን መጀመርያም ተናግሬ ነበር። የመጨረሻም የመጀመርያም የምትለው ቡድን የለም። ሁሉም ጠንካራ እና አጋጣሚውን አግኝቶ የሚጫወት ቡድን ነው።

ቡድኑ በመከላከል ወይስ በማጥቃቱ ድክመት የነበረበት ?

እነርሱ በመከላከሉ ላይ ተጫውተዋል በመልሶ ማጥቃት ነበር የሚሄዱት ክፍተት አልነበረውም። እስከ መጨረሻው ደቂቃ ጠብቀን ውጤቱን ይዘን ወጥተናል። ምክንያቱም ያገኘነውን አጋጣሚ ልንስተው እንችላለን። ግን እስከ መጨረሻው መሄዳችን ውጤቱን ይዘን ለመውጣት ተገደናል።

ከመሪው በአንድ ነጥብ መራቃቹ ወደ ዋንጫው እየቀረባችሁ ነው ?

ሁላችንም እንደ ቡድን እያሰብን ያለነው የዕለት የዕለት ጨዋታችንን እያሰብን የተሻለ ቦታ ለመድረስ ነው። ፋሲል አለ ሌላው አለ ብለን አስበን አይደለም። በራሳችን መንገድ እና ቅርፅ እሻነፍን በመሄድ ውጤቱ ወደፊት የሚገልፅ ይሆናል።

ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ አለበት። ከእኛ አራት ልጅ ተመርጠዋል። ብሔራዊ ቡድኑ የጋራችን የሁላችን ስለሆነ በድል እንዲመለሱ መልካም ምኞቴን እንገልፃለው።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጅማ አባ ጅፋር

ስለ ጨዋታው ሂደት

ጨዋታው በፈለግነው መንገድ ነው የሄደው። ጥሩ የመሸናነፍ መታገል የነበረበት ። ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሚታወቀው በአፍሪካ ታላቅ ቡድን ነው። ከእነርሱ ጋር ጥሩ የመሸናነፍ ፉክክር አድርገናል። ቡድናችን በሂደት መሻሻሎች ለውጦች አሉት። ግን ያደረግነው ጥሩ ነው።

በሁለት ጨዋታ በ80ኛ ደቂቃ ስለተቆጠረው

ምክንያት ማብዛት ነው የሚሆነው። ሽንፈት ሽንፈት ነው። የሚታዮ ስህተቶች አሉ የሚታዩ ለውጦችም አሉ። እነዛን ስህተቶች ለመቅረፍ ጊዜ ይፈልጋል። ከትልቁ ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረግነው ጨዋታ ጥሩ ነው።

ቡድንህ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ?

ተስፋ የሚቆርጠው የሞተ ሰው ብቻ ነው። ተስፋ የሚቆረጥ የሚባል አስተሳሰብ አይኖርም። ምክንያቱም ስራ ነው ሂደት ነው። ቡድኑ ላይ ለውጥ እንዳለው ለሁሉም የሚታይ ነው። እርማቶችን አድርገን ወደ ተሻለ ነገር እንደምንመጣ ተስፋ አደርጋለው።

በዳኝነት ጉዳይ ጥያቄ አለህ ?

ዳኝነትን በተመለከተ የምናገረው ነገር የለም። እረዳለው ስህተቶችን ጠንቅቄ እረዳለው። ዳኝነትን በሚመለከት መውቀስ ስለማልፈልግ። ውጤቱን በፀጋ ከመቀበል ውጭ ምንም ማድረግ እችላለው። ምስሉን እየተመለከትኩኝ ለኳሱም ቅርብ ስለነበርኩኝ አይቸዋለው።ዳኛን ከማክበር ውጭ ምንም የምለው ነገር የለም።

ብሔራዊ ቡድን በተመለከተ

ብሔራዊ ቡድናችን ያለው ተነሳሽነት በጣም ጥሩ ነው። በማጣርያ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት ጥሩ ነው። ስለዚህ ትልቅ ውጤት ያመጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለው። መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ለቡድኑም ለህዝቡም እመኛለው።