መቻል በቀሪ የሊጉ ሳምንታት በጉዳት ምክንያት ወሳኝ ተጫዋቹን አያገኝም

ባሳለፍነው ሳምንት ከበድ ያለ ጉዳት የገጠመው የመቻሉ አማካይ ለረጅም ወራት ከሜዳ ይርቃል።

\"\"

በአስራ ሰባተኛው ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ከ መቻል ባደረጉት ጨዋታ ገና በጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ ፍፁም ዓለሙ ከበድ ያለ ጉዳት ደርሶበት ጨዋታውን መቀጠል ሳይችል እንደወጣ አይዘነጋም።

ለተሻለ ህክምና በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታል ያመራው ፍፁም ዓለሙ ከጉልበቱ በታች በሚገኘው አጥንቱ ላይ የመሰንጠቅ አደጋ እንደደረሰበት አውቀናል። በአሁኑ ሰዓት እግሩ ላይ ጀሶ የገባለት ሲሆን ከተጫዋቹ እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ በዚህ ዓመት ለቡድኑ አገልግሎት እንደማይሰጥ እና በትውልድ ከተማው እንደሚገኝ አውቀናል።

በደረጃ ሠንጠረዡ ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቻል ወሳኝ ተጫዋቹን ግልጋሎት በቀሪው የሊጉ ጨዋታዎች ላይ የማይገኝ መሆኑን ቡድኑን ይጎዳዋል ተብሎ ይገመታል።

\"\"