የአፍሪካ ዋንጫ ልዩ ዘገባ ከካሜሩን | ግብጠባቂው ለቀጣይ ጨዋታዎች ይደርስ ይሆን ?

በጉዳት ምክንያት ከመጀመርያው ጨዋታ ውጪ የነበረው ግብጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤል በቀጣይ ጨዋታዎች ይደርስ ይሆን ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመራጭ በመሆን በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈው ግብጠባቂው ፋሲል ገ/ሚካኤል ብሔራዊ ቡድኑ ያውንዴ ለዝግጅት ከከተመበት ጊዜ አንስቶ ልምምዱን ሲሰራ ቢቆይም የትከሻ ላይ ጉዳት አጋጥሞት እንደነበረ በተለያዩ ዘገባዎቻችን ስንገልፅ ቆይተናል።

 

የመጀመርያው ጨዋታ በዚሁ ጉዳት ምክንያት ያመለጠው ፋሲል በቀጣይ ጨዋታዎች እንዲደርስ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ትናንት ወደ ሆስፒታል በማምራት የራጅ ምርመራ አድርጎ በውጤቱም ትከሻው ላይ ውልቃት እንዳለበት ተነግሮታል። ይህን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም በህክምና ክፍሉ ልምምድ እንዲያቋርጥ ተነግሮት እረፍት እንዲያደርግ ተደርጓል።

ፋሲል በቀጣይ ሐሙስ ከካሜሩን ጋር በሚኖረው ጨዋታ የመድረሱ ነገር ያከተመ ሲሆን ምን አልባት ከጉዳቱ እያገገመ የሚሄድ ከሆነ ለቡርኪና ፋሶ ጨዋታ እንደሚደርስ መገመቱን ሰምተናል።