ካርሎስ ዳምጠው ወደ አዲስ ክለብ ተዘዋውሯል

በአጥቂ እና አማካይ ቦታ ላይ ሲጫወት የሚታወቀው ካርሎስ ዳምጠው ከደቂቃዎች በፊት ወደ አዲስ ክለብ የሚያደርገውን ዝውውር ቋጭቷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በለገጣፎ ለገዳዲ ያሳለፈው ቁመታሙ ካርሎስ ዳምጠው ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሏል። ከሳምንታት በፊት ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሜ ለመስራት ተቃርቦ የነበረው ይህ ተጫዋች ትላንት ከብርቱካናማዎቹ ክለብ አመራሮች ጋር ካደረገው የተሳካ ድርድር በኋላ ዛሬ ቡድኑን ለመቀላቀል ፌራማውን አኑሯል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ለገጣፎ ለገዳዲን በአምበልነት መርቶ አምስት ግቦችን ያስቆጠረው ይህ ተጫዋች በተለያዩ ቦታዎች ተሰልፎ ቡድኑን በቋሚነት ማገልገሉ ይታወቃል። መቻል፣ አውስኮድ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ወልዋሎ የተጫዋቹ የቀድሞ ክለቦች ናቸው።