ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የጀመረው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የመስመር አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በርከት ያሉ ዝውውሮችን በመፈፀም ጠንካራ ቡድን ለመስራት እየተጋ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመስመር አጥቂውን ኤፍሬም ታምሩን ማስፈረማቸው ታውቋል።

ከዚህ ቀደም በከንባታ ሺንሺቾ ሲጫወት የነበረው ኤፍሬም በዘንድሮ ከፍተኛ ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኝበት ምድብ ለ በቤንች ማጂ ቡና ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የቆየ ሲሆን ተጫዋቹን አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ሲከታተሉት ቆይተው በመጨረሻም ዛሬ ማስፈረማቸው ታውቋል።