ኢትዮጵያ መድን የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ተገልጿል

የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌው ኢትዮጵያ መድን በአዳማ ከተማ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደገ በኋላ በተሻለ ቁመና ላይ ሆኖ ሊጉን በሦስተኛ ደረጃነት ያጠናቀቀው የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌው ኢትዮጵያ መድን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ከክለቡ በለቀቁ ተጫዋቾች ምትክ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ እንደ ተመስገን ዮሐንስ ፣ ንጋቱ ገብረስላሴ ፣ አዲስ ተስፋዬ ፣ አቡበከር ወንድሙ እና ሙሴ ከቤላን ያስፈረመ ሲሆን ውል ያጠናቀቁ ተጫዋቾችን ኮንትራትም ማራዘሙ ይታወሳል። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን በደረሳት መረጃ መሠረት ደግሞ ክለቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ሊጀምር ነው።

በዚህም የክለቡ ተጫዋቾች የፊታችን እሁድ ነሀሴ 7 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴል ከተሰባሰቡ በኋላ በማግስቱ ሰኞ ወደ አዳማ በማምራት ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል።