አዳማ ከተማ ሰባተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

አዳማ ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመራው አዳማ ከተማ በዝውውር መስኮቱ በለቀቃቸው ወሳኝ ተጫዋቾች ምትክ ሊሆኑ የሚችሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኝ ሲሆን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አቡበከር ሻሚልን በማስፈረም የክለቡን አዳዲስ ፈራሚዎች ቁጥር ሰባት አድርሶታል።

ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ሊጉ ኮልፌ ቀራኒዮ የተጫወተው እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታን ያደረገው ተጫዋቹ ቀጣይ ማረፊያው አዳማ ሆኗል።