ሲዳማ ቡና ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ የሚመመራው ሲዳማ ቡና የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምርበትን ቀን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከሚሊኒየሙ ወዲህ መሳተፍ የጀመረው ሲዳማ ቡና በ2016 የሊጉ ተሳትፎው የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ አማካኝነት ወደ ዝውውሩ በመግባት እስከ አሁን ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን ፣ አብዱራህማን ሙባረክ ፣ ብርሀኑ በቀለ ፣ ደስታ ዮሐንስ እና ዮሴፍ ዮሐንስን የስብስቡ አካል ያደረገ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገር ውስጥ እና የውጪ ተጫዋቾችን ከማስፈረሙ አስቀድሞ ዝግጅት የሚጀምርበትን ቀን ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቋል።

በዚህም መሠረት ከፊታችን ነሀሴ 9 ጀምሮ በሀዋሳ ታደሰ እንጆሪ ሆቴል የክለቡ አባላት ከተሰባሰቡ በኋላ በማግስቱ ነሀሴ 10 ዕለተ ረቡዕ ላይ የቅድመ ዝግጅት ልምምዳቸውን ይጀምራሉ።