የሚሊዮን ሠለሞን ማረፊያው ታውቋል

በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው የመሐል ተከላካዩ በአንድ ዓመት ውል ሀዋሳ ከተማን ተቀላቅሏል።

ለ2016ቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በተሻለ ደረጃ ላይ ሆኖ ለመገኘት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ታፈሰ ሠለሞን ፣ አማኑኤል ጎበና ፣ ፂሆን መርዕድ እና እንየው ካሳሁንን ያስፈረሙት ሀዋሳ ከተማዎች ከሦስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረውን የመሐል ተከላካዩ ሚሊዮን ሠለሞንን በአንድ ዓመት ውል በይፋ ስለ ማስፈማቸው ሶከር ኢትዮጵያ በተለይ የደረሳት መረጃ ያመላክታል።

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች የሆነው ሚሊዮን ከ2013 ጀምሮ እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድረስ በአዳማ ከተማ ሲጫወት ካሳለፈ በኋላ በሲዳማ እና አዳማ ያሰለጠኑትን አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ጥሪ ተቀብሎ ረፋድ ላይ ማረፊያውን ሀዋሳ አድርጓል።