የጦና ንቦቹ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ታውቋል

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹን በዋና አሰልጣኝነት መንበር የሾሙት ወላይታ ድቻዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት መጀመሪያ ቀናቸው ታውቋል።

ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ክለቡን እንዲያሰለጥኑ አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹን ወደ ሀላፊነት ካመጡ በኋላ በክለቡ ውላቸው የተጠናቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾችን ኮንትራት ያራዘሙት ወላይታ ድቻዎች የዝውውር መስኮቱን ተጠቅመው ባዬ ገዛኸኝ ፣ አብነት ደምሴ ፣ ፀጋዬ ብርሀኑ ፣ ብዙአየው ሰይፈ እና ፍፁም ግርማን ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉ ሲሆን በቀጣይ ባሉ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ከማካተታቸው በፊት ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚገቡበትን ቀን ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቀዋል።

ክለቡ እንደገለፀልን ከሆነ ከፊታችን ረቡዕ ነሀሴ 10 ጀምሮ በክለቡ መቀመጫ ሶዶ ከተማ ላይ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።