አዳማ ከተማ ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ይፋ ሆኗል

አዳማ ከተማ በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ እየተመራ በክለቡ መቀመጫ ከተማ ዝግጅት መቼ እንደሚጀምር ዝግጅት ክፍላችን አውቃለች።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፈው አዳማ ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የነበሩ ወሳኝ ተጫዋቾችን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ ከሰጠ በኋላ በአንፃሩ በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ እየተመራ በለቀቁ ተጫዋቾች ምትክ ሊሆኑ የሚችሉ ወደ ሰባት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል። በዚህም ሱራፌል ዐወል ፣ አሸናፊ ኤልያስ ፣ ፍቅሩ አለማየሁ ፣ መላኩ ኤልያስ ፣ ተክለማርያም ሻንቆ ፣ ኤፍሬም ዘካሪያስ እና አቡበከር ሻሚልን የቀጣዩ ዓመት አካል ያደረገው ቡድኑ በቀጣዮቹ ቀናት ከሚያስፈርሟቸው ተጨማሪ ተጫዋቾች በፊት የ2016 የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን መቼ እንደሚጀምሩ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

እንደ ክለቡ ገለፃ ከሆነ የፊታችን ረቡዕ ነሀሴ 10 የክለቡ አጠቃላይ አባላት በአዳማ ራስ ሆቴል ከተሰባሰቡ በኋላ ዕለተ ሐሙስ ነሀሴ 11 በይፋ የቅድመ ውድድር ጅግጅታቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።