ዐፄዎቹ ዝግጅት የሚጀምሩበትን ቀን አስታውቀዋል

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በድጋሚ በአሰልጣኝነት የሾሙት ፋሲል ከነማዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምሩበትን ቀን ይፋ አድርገዋል።

የተጠናቀቀውን የፕሪምየር ሊግ ቆይታቸውን ካለፉትን ዓመታት አንፃር ተዳክመው የቋጩት ፋሲል ከነማዎች በ2016 የውድድር ዘመን በተሻለ ቁመና ላይ ለመገኘት አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በድጋሚ የክለቡ ዋና አለቃ በማድረግ የቀጠሩ ሲሆን በመቀጠል እንደ ቃልኪዳን ዘላለም ፣ ምኞት ደበበ ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል ፣ እዮብ ማቲያስ እና ጌታነህ ከበደን በይፋ ወደ ክለባቸው መቀላቀላቸው ይታወቃል። በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ አዳዲስ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ተጫዋቾችን ከማስፈረማቸው በፊትም የቅድመ ውድድር ዝግጅቱ መቼ እና የት እንደሚጀምር ይፋ ሆኗል።

በዚህም ከፊታችን ሐሙስ ነሀሴ 11 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ታደሰ እንጆሪ ሆቴል ማረፊያቸውን በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚያከናውኑ ተጠቁሟል።