ቡናማዎቹ አማካይ አስፈርመዋል

ኢትዮጵያ ቡና የአማካይ መስመር ተጫዋች በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል።

በአሠልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪችን የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በዝውውር መስኮቱ ግብ ጠባቂው አስራት ሚሻሞን ማስፈረማቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ አማካይ መስመር በማዞር ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የቀድሞ መከላከያ(መቻል)፣ ወልዲያ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ወልቂጤ ከተማ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ለገጣፎ ለገዳዲ አምርቶ የተጫወተ ሲሆን አሁን በሁለት ዓመት ውል ቡናማዎቹን ተቀላቅሏል።