ድሬዳዋ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የነባሮችን ውልም አድሷል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፈው ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮቹንም ውል አራዝሟል።

በአሰልጣኝ እዮብ ተዋበ የሚመሩት የድሬዳዋ ሴት እግር ኳስ ቡድን በፕሪምየር ሊጉ ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ ከቀናቶች በፊት በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን የነባሮችንም ውል ሲያራዝሙ እንደነበር ይታወሳል። ቡድኑ ሁለት አዳዲስ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአምስቱን ኮንትራት አድሷል።

ክለቡ የመሐል ተከላካዩዋን ፍሬወይኒ አበራን ከንፋስ ስልክ እና አጥቂዋን ረድኤት ዳንኤልን ከልደታ ሲያስፈርም የሊና መሐመድ ፣ አያን ሙሳ ፣ ጥሩዬ ምስጋና ፣ ዕድላዊት ለማ እና ሀዳስ ዝናቡን ውል አድሷል።