ሻሸመኔ ከተማ የአምስት ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉ አምስት ተጫዋቾች ውል ተራዝሟል።

ለ2016ቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ራሱን እያጠናከር የሚገኘው አዲስ አዳጊው ሻሸመኔ ከተማ እስካሁን በድምሩ ወደ ሰባት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾች ያስፈረመ ሲሆን የሁለት ነባሮችን ውል ማራዘሙም ይታወሳል። አሁን ደግሞ ቡድኑን ከታችኛው የሊጉ ዕርከን ወደ ከፍተኛው የሀገሪቱ ሊግ ያሳደጉ አምስት ተጫዋቾች ውላቸው ታድሶላቸዋል።

በቡድኑ ውስጥ በተከታታይ ዓመታት ቆይታን ያደረገው የቀድሞው የሰበታ እና አዳማ አማካይ አዲስዓለም ደሳለኝ ፣ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ወጋየሁ ቡርቃ ፣ የቀድሞው የአቃቂ አማካይ ሳምሶን ተሾመ ፣ በሁለተኛው ዙር ቡድኑን ተቀላቅለው የነበሩት የመስመር ተጫዋቾቹ ፉዓድ መሐመድ እና አብዱልከሪም ቃሲም በክለቡ ውል ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች ናቸው።