ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ ዱራሜ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙን ያሰናበተው የከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ክለብ ሀምበሪቾ ዱራሜ ተመስገን ዳናን በቦታው ተክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን የመጀመሪያውን ዙር የጅማ ውድድር ላይ ካለፈው ዓመት አንፃር ዝቅተኛ ውጤት በማምጣት በምድብ ሐ በደረጃ ሰንጠረዡ ስድስተኛ ደረጃ ላይ በአስር ነጥቦች ለመቀመጥ የተገደደው ሀምበሪቾ ዱራሜ ከአሰልጣኝ ዳዊት ጋር ቀሪ የስድስት ወራት ውል ቢኖረውም በውጤት መጥፋት የተነሳ አሰልጣኙን በማሰናበት በምትኩ ተመስገን ዳናን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል፡፡

የአሰልጣኝነት ህይወቱን በሀዋሳ ከተማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች በማሰልጠን በተደጋጋሚ በሁለቱም የዕድሜ ዕርከኖች በተደረጉ የፕሪምየር ሊግ ውድድሮ ሻምፒዮን በመሆን በወጣቶች ላይ ሲሰራ የሚታወቀው አሰልጣኙ የኢትዮጵያ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖችንም በመያዝ የተሳካ ጊዜ አሳልፏል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ረዳት እና የደቡብ ፖሊስ ዋና አሰልጣኝ በመሆን የሰራው ተመስገን ያለፉትን ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀምበሪቾ ዱራሜን አሰልጣኝ ተደርጎ መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች፡፡