ብሄራዊ ቡድኑ በአልጄርያ የመጀመርያ ልምምዱን ሰርቷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከረጅም ጉዞ በኋላ ትላንት አልጄርያ ብሊዳ ከተማ በመግባት ወደተዘጋጀላቸው ሆቴል አምርተው እረፍት ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለት የመጀመርያ ልምምዳቸውን አድርገዋል፡፡

የዛሬውን ልምምድ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 12፡00 ጀምረው 01፡30 ላይ ሲያጠናቅቁ ወደ አልጄርያ የተጓዙት ሁሉም ተጫዋቾች ልምምድ ሰርተዋል፡፡ በአልጄርያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ሰለሞን በልምምድ ቦታው በመገኘት ተጫዋቾቹን ማበረታታቸውም ታውቋል፡፡

ቡድኑ ልምምድ ያደረገበት ሜዳ በሆቴሉ አቅራብያ የሚገኝ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን በአልጄርያ ወቅታዊው የአየር ንብረት ቀዝቃዛ ነው ተብሏል፡፡ በነገው እለትም ጨዋታውን በሚያደርግበት ስታደ ሙስጣፋ ልምምዱን እንደሚያደርግ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የአልጄርያ እና የኢትዮጵያ ጨዋታ አርብ ምሽት 04፡30 ላይ በብሊዳ ስታደ ምስጠፋ ቻክር ይካሄዳል፡፡

PicsArt_1458756327003 PicsArt_1458756466248

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *