​ሰበታ ከተማ ከሁለት ተጫዋቾች ጋር ተለያየ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊው ክለብ ሰበታ ከተማ ከሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የአስራ ሦስት ሳምንታት ጉዞው ያልሰመረለት ሰበታ ከተማ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ካገደ በኋላ በዛሬው ዕለት የተወደደበትን ሦስት ነጥብ ለማግኘት በበብቸኝነት በረዳት አሰልጣኙ ብርሀን ደበሌ እየተመራ ከባህር ዳር ከተማ ጋር የአስራ አራተኛ ሳምንት ጨዋታውን ያከናውናል፡፡

በሲዳማ ጎፈሬ ዋንቻ ውድድር ላይ ጉዳት በማስተናገዱ ከረጅም ጊዜ በኋላ በቅርቡ ወደ ሜዳ የተመለሰው የቀድሞው የመከላከያ ወጣት አጥቂ መሐመድ አበራ እና በበርካታ ክለቦች የምናውቀው አማካዩ ፍፁም ተፈሪ ለክለቡ ካቀረቡት የልቀቁኝ ደብዳቤ መነሻነት ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ከሁለቱም አካላት አረጋግጣለች፡፡

ድረ-ገፃችን አሁን እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ከመስመር አጥቂው ዮናስ አቡሌ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ለመለያየት ከጫፍ የደረሱ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችም ከክለቡ ጋር ሊለያዩ እንደሚችሉ ሰምተናል።