​ወልቂጤ ከተማ የአማካዩን ውል አራዘመ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በወልቂጤ ውሉን ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

አሠልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን ካገደ በኋላ በተመስገን ዳና እየተመራ በ13ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከሲዳማ ቡና ጋር ከቀናተ በፊት ነጥብ የተጋራው ወልቂጤ ከተማ ውሉ ተጠናቆ የነበረውን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ለተጨማሪ አንድ አመት በክለቡ እንዲቆይ አድርጓል።

የቀድሞው የመከላከያ ፣ ደደቢት እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች ለቀጣዮቹ አስራ ሁለት ወራት በሰራተኞቹ ቤት ዳግም የሚያሳልፍ ይሆናል፡፡