​አዲስ አበባ ከተማ ከመስመር ተጫዋቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ከቀናት በፊት ከአማካዩ ጋብሬል አህመድ ጋር የተለያየው የመዲናው ክለብ ከሌላ ተጫዋች ጋርም በስምምነት ተለያይቷል።

ዘንድሮ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ዳግም የተቀላቀለው አዲስ አበባ ከተማ በአሠልጣኝ እስማኤል እየተመራ ውድድሩን ቢጀምርም ካሳደጉት አሠልጣኝ ጋር ተለያይቶ በደምሰው ፍቃዱ እየተመራ ውድድሩን ማገባደዱ ይታወቃል። በ15 ጨዋታዎች 14 ነጥቦችን በመሰብሰብ 14ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ክለቡም ከሦስት ቀናት በኋላ ለሁለተኛው ዙር ውድድር ዝግጅቱን አዳማ ላይ ለመጀመር እየተሰናዳ ሲሆን በዝውውር ገበያውም ለመሳተፍ እየጣረ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም በሰራነው ዘገባ ጋብሬል አህመድ ክለቡን እንደተለያየ ገልፀን የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሌላኛው የመስመር ተጫዋች ያሬድ ሀሰን ጋር መለያየቱ እርግጥ ሆኗል። ክረምት ላይ ስብስቡን የተቀላቀለው የቀድሞ የወልዲያ፣ ድሬዳዋ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች ዘንድሮ ለአዲስ አበባ ለ741 ደቂቃዎች ግልጋሎት ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ቀሪ የ6 ወር ኮንትራት እየቀረው በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።