ድሬዳዋ ከተማ የቀድሞ የቡድኑ የግራ መስመር ተከላካይን አስፈረመ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የመጀመሪያ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያው ዙር ደካማ የውድድር ጊዜን ያሳለፈው ድሬዳዋ ከተማ በርካታ ለውጦችን በማድረግ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የቀድሞው የክለቡ ተጫዋች የነበረውን አማረ በቀለን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ወልድያ እና ድሬዳዋ ከተማ የግራ መስመር ተከላካይ የነበረው አማረ በቀለ ከአንድ አመት በፊት ድሬዳዋን ከለቀቀ በኋላ ያለ ክለብ ያሳለፈ ሲሆን በሁለተኛው ዙር የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ወደ ምስራቁ ክለብ በድጋሚ ተመልሶ የአንድ አመት ውልን ፈርሟል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናቶችም ድሬዳዋ ከተማ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች የሚያስፈርም ይሆናል፡፡