የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን አልተቀላቀሉም

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

መጋቢት 16 ከኮሞሮስ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ በትናንትናው ዕለት የተሰባሰበው ዋልያው ከኢትዮጵያ ቡና የጠራቸውን 5 ተጫዋቾች አላገኘም።

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳምንት በኋላ ወደ ኮሞሮስ በማቅናት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ እንዳቀረበ ይታወቃል። ተጫዋቾቹም ትናንት ከ8 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል የተሰባሰቡ ሲሆን የኮቪድ-19 ምርመራም ተደርጎላቸዋል። በዛሬው ዕለት ደግሞ የሜዳ ላይ የምዘና ስራዎች እንደሚከናወኑ የሰማን ሲሆን ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ግን የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች ስብስቡን እንዳልተቀላቀሉ የዝግጅት ክፍላችን አውቃለች።

ከቡና የተጠሩት አቤል ማሞ፣ አስራት ቱንጆ፣ አማኑኤል ዮሐንስ፣ ዊሊያም ሰለሞን እና አቡበከር ናስር በአሁኑ ሰዓት ከክለባቸው ጋር ልምምድ እያከናወኑ ሲገኝ የብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ የአቋም መለኪያ ስለሆነ ጨዋታው ሲቃረብ ወደ ቡድኑ እንዲያመሩ እስከዛ ከክለባቸው ጋር ልምምዳቸውን እየሰሩ እንዲቆዩ ቡና አቋም እንደያዘ ሰምተናል። ምናልባት አዲስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ በሁለት እና ሦስት ቀናት ውስጥ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚሄዱም ይጠበቃል።