የብሔራዊ በድኑ አሰላለፍ ታውቋል


10:00 ላይ ከዩጋንዳ አቻው ጋር የማጣሪያ ጨዋታ ያለበት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

በሕንድ ለሚደረገው የ2022 የሴቶች የ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ 10:00 ላይ በአበበ በቂላ ስታዲየም ከዩጋንዳ ጋር የመልስ ጨዋታ ይጠብቀዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት በመጀመሪያው ጨዋታ ከመመራት ተነስቶ 2-2 ጨዋታውን የጨረሰው ቡድኑ በዛሬው ጨዋታ የሚጠቀመውን አሰላለፍ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከመጀመሪያው ጨዋታ አንፃር ሦስት ለውጦች ሲደረጉ ሜላት ዓሊሙዝ ፣ መስከረም መኮንን እና እየሩስ ወንድሙ በትርሲት ወንድወሰን ፣ ቃልኪዳን ወንድሙ እና ሰብለወንጌል ወዳጆ ምትክ ጨዋታውን ይጀምራሉ። የአሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ ቡድን የዛሬ የመጀመሪያ አሰላለፍ እንደሚከተለው መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ግብ ጠባቂ

አበባ አጄቦ

ተከላካዮች

ፀሀይነሽ ጁላ
መሰረት ማሞ
ድርሻዬ መንዛ
መታሰቢያ ክፍሌ

አማካዮች

መስከረም መኮንን
ትዕግስት አዳነ

የምወድሽ አሸብር
ሜላት ዓሊሙዝ
እየሩስ ወንድሙ

አጥቂ

እሙሽ ዳንኤል