የዋልያዎቹ አሰላለፍ ታውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]


ከኮሞሮስ አቻቸው ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል።

በዓለም አቀፍ ይፋዊ የብሔራዊ ቡድኖች የጨዋታ ወቅት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ኮሞሮስ ከትናንት በስትያ ያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ ጨዋታውን ያከናውናል። የቡድኑ አሠልጣኝ ለጨዋታው የሚጠቀሙትን የመጀመሪያ አሰላለፍም ሶከር ኢትዮጵያ ደርሷታል።

11:00 ሰዓት ሲል በቱኒዚያዊው ዳኛ ናስር ሳሉም የሚመራው ጨዋታ በስታድ ኦምኒስፖርትስ ማሉዚኒ ሲደረግ ዋልያው የሚጠቀመው አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

23 ፋልሲ ገብረሚካኤል
21 አስራት ቱንጆ
4 ምኞት ደበበ
16 ያሬድ ባየህ
20 ረመዳን የሱፍ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
7 ሱራፌል ዳኛቸው
18 ሽመልስ በቀለ
17 ዳዋ ሆቴሳ
11 አማኑኤል ገብረሚካኤል
10 አቡበከር ናስር