የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ከደቡብ አፍሪካ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ የሚጠብቀው የአሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ ስብስብ ይፋ ተድርጓል።

በሕንድ በሚደረገው የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ላይ ይገኛል። ቡድኑ በመጀመሪያ ጨዋታው ዩጋንዳን በድምር የደርሶ መልስ ውጤት ጥሎ ማለፍ የቻለ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የሚገናኝ ይሆናል። ለዚህ ጨዋታ ከነገ ጀምሮ ዝግጅቱን የሚጀምረው የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብም ታውቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳሳወቀው አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የደቡብ አፍሪካውን ጨዋታ ታሳቢ በማድረግ ለ 27 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። አሰልጣኙ ዩጋንዳን ጥሎ ያለፈው ቡድናቸው ከያዘው ስብስብ ላይ ተጨማሪ ተጫዋቾችን መምረጣቸውን ፌዴሬሽኑ ጨምሮ አስታውቋል። አዲስ የተመረጡት ተጨዋቾች በዚህ ዓመት ከተጀመረው የፌዴሬሽኑ ፓይለት ፕሮጀክት ውስጥ ከዲላ እና ድሬዳዋ ፕሮጀክቶች የተወሰዱ መሆናቸውም ይፋ ተደርጓል።

የተመረጡት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው :-

ከኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ – አበባ አጅቦ እና ብዙነሽ ባልቻ

ከቅዱስ ጊዮርስ- ሰናይታ ሸጎ ፣ ንግሥት አስረስ እና እየሩስ ወንድሙ

ከጌዴኦ ዲላ – መታሰብያ ክፍሌ ፣ ሠሚራ ከድር እና ሠብለወንጌል ወዳጆ

ከአርባምንጭ ከተማ – ድርሻዬ መንዛ እና ቅዕግስት አዳነ

ከቦሌ ክፍለ ከተማ – ትርሲት ወንድወሰን ፣ ሜላት አሊሙዝ እና ሥንታየው ኢርኮ

ከሀዋሳ ከተማ – ፀሐይነሽ በቀለ ፣ ቃልኪዳን ወንድሙ እና እሙሽ ዳንኤል

ከሰበታ ከተማ – እየሩሳሌም ወሰኔ

ከአምቦ አካዳሚ – ሸዊት ብርሃኔ

ከሀምበሪቾ – መሰረት ማሞ

ከአዳማ ከተማ – ደመቀች ዳልጋ

ከድሬዳዋ ከተማ – ትሁን አየለ

ከኢትዮ ኤሌእትሪክ – ትንቢት ሳሙኤል

ከአዲስ አበባ ከተማ – የምወድሽ አሸብር

ከኢፉፌ ዲላ ፓይለት ፕሮጀክት- ምትኬ ብርሃኑ

ከኢፉፌ ድሬዳዋ ፓይለት ፕሮጀክት – ሊዲያ ሰለሞን ፣ በአምላክ ገረመው እና ህሊና ካሣሁን