ፀሀይነሽ አበበ እና ረዳቶቿ ወደ ብሩንዲ ያቀናሉ

አራት ኢትዮጵያዊያን እንስት ዳኞች የዓለም ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን ይመራሉ፡፡

በህንድ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመካፈል ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በማጣሪያው ጨዋታዎችን እያደረጉ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በማጣሪያው በቀጣይ ደቡብ አፍሪካን ስትገጥም የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፉት ብሩንዲ እና ታንዛኒያ ደግሞ ቡጁንቡራ ላይ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ 10፡00 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ። ይህንንም ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊ ሴት ዳኞች እንዲመሩት ካፍ መመደቡን አውቀናል፡፡

በዚህም ፀሀይነሽ አበበ በመሀል ዳኝነት ጨዋታውን ስትመራው በረዳትነት ደግሞ ወይንሸት አበራ እና ከወሊድ መልስ ወደ ዳኝነት የተመለሰችው ወጋየሁ ዘውዴ እንዲሁም ምስጋና ጥላሁን በአራተኛ ዳኝነት በጨዋታው ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

*ትናንት ምሽት ምስጋና ጥላሁን ዋና ፀሀይነሽ አበራ ደግሞ አራተኛ ዳኛ መሆናቸውን የጠቆምንበት ዘገባ ላይ ስህተት በመፈፀማችን ባለጉዳዮቹን እና አንባቢዎቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።