አሠልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ ከድሉ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል

የደቡብ አፍሪካ አቻውን ሦስት ለምንም የረታው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ከጨዋታው በኋላ አጠር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል።

ጨዋታው እንዴት ነበር?

ጨዋታው እንደጠበቅነው ነው የሆነው። መጀመሪያም በማጥቃት ላይ ነው የምንጫወተው ብለን ተናግረን ነበር። እንደ ጠበቅነውም አሸንፈን ወጥተናል። በዚህም በጣም ደስ ብሎናል።

እየመሩ በሁለተኛው አጋማሽ ስላደረጓቸው ለውጦችች?

ጨዋታውን እዚሁ ጨርሰን ነው መሄድ የፈለግነው። ምክንያቱም አዲስ አበባ ላይ ቀለል አድርገን ለመጫወት። ለዚህ ደግሞ እዚህ አግብተን መሄድ አለብን። ይህንን ተከትሎ ከመከላከል ይልቅ ለማጥቃት ነው ያሰብነው። ለውጦቹንም ያደረግነው ለማሸነፍ ስላሰብን ነው።

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድንን የመከላከል ችግር ስለተጠቀሙበት መንገድ?

እኛ የደቡብ አፍሪካን ጨዋታ ከዚህ በፊት አይተን አናውቅም። እንዳልኩት ግን ለማሸነፍ እና ለማሸነፍ ብቻ ወደ ሜዳ ስለገባን የቡድኑን ጠንካራ እና ደካማ ጎን አላየንም። እኛ ወደ ሜዳ የገባነው የራሳችንን ሥራ ለመስራት ነው።