ሊጉ ለከርሞው የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቀጣዩ ዓመት መች እንደሚጀምር ይፋ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የሚመራው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 24ኛው ሳምንት ላይ ደርሷል። ዘንድሮ ፍፃሜውን በባህር ዳር ከተማ የሚያደርገው ውድድሩ ከ25ኛው ሳምንት በኋላ ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ተቋርጦ በድጋሚ በመቀጠል በመጪው ወር ሰኔ 24 ላይ ፍፃሜውን እንደሚያገኝ ይጠበቃል።

አክሲዮን ማህበሩ አሁን ይፋ ባደረገው መሰረት ደግሞ የቀጣዩን ዓመት ውድድር ቀደም ብሎ ለመጀመር አስቧል። በዚህም የ2015ቱ ውድድር መስከረም 20 ላይ እንደሚጀመር ተነግሯል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሐምሌ 1 እንደሚከፈትም ታውቋል።