የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 0-1 አዲስ አበባ ከተማ

ብዙዓየሁ ሰይፈ በመጨረሻው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ አዲስ አበባ ከተማ በመጨረሻም ወላይታ ድቻን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ጳውሎስ ጌታቸው – አዲስ አበባ ከተማ

በውጤቱ ደስተኛ ስለመሆኑ

“ከታችኛው ቀጠና ባያወጣንም ቀጣይ ጨዋታዎችን በጥንቃቄ እንድናደርግ ያደርገናል ፤ ሌላኛው ልጆቹን በስነልቦና ገንብተን የተሻለ ነገር ለመስራት እንደመምጣቴ የተሻለ ነገር ሰርተናል ብዬ አስባለሁ።”

በመስመር በኩል ስለነበራቸው እንቅስቃሴ

“ገና ከጅምሩ በአየር ላይ አጠቃቀም የተሻሉ እንደሆኑ ስለተረዳን በረጅም ኳስ መጠቀም ጥቅም እንደሌለው ተገንዝበን ነበር ስለዚህ በመስመር የተጠቀምናቸው ተጫዋቾች በሙሉ የተሻለ ተንቀሳቅሰዋል ብዬ አስባለሁ።ዋናው ግን በዛሬው ጨዋታ የተሳካልን ነገር ስንታየሁ መንግሦቱ በበቂ መልኩ ኳስ እንዳያገኝ ያደረግነው ጥረት ውጤታማ አድርጎናል ብዬ አስባለሁ።”

ስለ ጨዋታ እንቅስቃሴያቸው

“ጨዋታውን ማሸነፍ እና መሸነፍ ከሚፈጥረው ተፅዕኖ አንፃር ከእንቅስቃሴ ይልቅ ለውጤት ትኩረት ሰጥተን ተጫውተናል።”

ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወላይታ ድቻ

ስለጨዋታው

“ጨዋታው አሸንፈን ደረጃችን ለማሻሻል የነበረን ፍላጎት ሜዳ ላይ የታየ ነበር ፤ ነገርግን በማጥቃቱ ረገድ የነበረን ነገር መሻሻል ያስፈልገናል።አዲስ አበባ ከዚህ ቀደም በነበረው እንቅስቃሴ እንደ ቡድን ጥሩ እየተንቀሳቀሰ በጊዜ አጠቃቀም ችግር እየተሸነፈ የነበረ ቡድን ነበር ነገርግን ዛሬ በተቃራኒው ሆኗል ከጅምሩ እንደሚያስቸግሩን አስበን ነበር ያንንም ነው የተመለከትነው።”

በመጀመሪያው አጋማሽ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ስላለመቻላቸው

“በጨዋታው በአጠቃላይ በማጥቃቱ ረገድ የነበረን ነገር ጥሩ አልነበረም ፤ ልጆቹ ከጉዳት የተመለሱ እንደመሆናቸው ወደ ሙሉ አቅማቸው እሲከመለሱ ድረስ ጊዜ ይወስዳል።