አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን ሸኝቷል

ከወረጅ ቀጠናው ለመውጣት እየጣረ የሚገኘው አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን በዲሲፕሊን ምክንያት ከስብስቡ መቀነሱ ታውቋል።

በ28ኛ ሳምንት ከመከላከያ ጋር ያለ ጎል አቻ ያጠናቀቀው አዳማ ከተማ በተደጋጋሚ የዲሲፒሊን ጥሰት ፈፅመዋል ያላቸውን ተጫዋቾች ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ መሸኘቱ ተገልጿል። የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ተጫዋቾች ተከላካዩ ቶማስ ስምረቱ እና አማካዩ ዮናስ ገረመው ናቸው። ክለቡ ተጫዋቾቹን ለጊዜው ከባህር ዳር ያሰናብታቸው እንጂ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚያስተላልፍ ሰምተናል።

ትናንት ተጫዋቾቹን ያልተጠቀመው አዳማ በቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ላይም እንደማይጠቀምባቸው ታውቋል።