ቡናማዎቹ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል

የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ዛሬ ሲከፈት ኢትዮጵያ ቡናም የመጀመሪያ ሁለት ተጫዋቾቹን የግሉ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከዛሬ ሀምሌ 1 እስከ መስከረም 19 ድረስ እንደሚቆይ ይታወቃል። መስኮቱ ገና ከሰዓታት በፊት ሲከፈት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ፈራሚውን ይፋ አድርጓል። በዚህም የአማካይ መስመር ተጫዋቹን አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ እና የመስመር ተከላካዩ ኃይለሚካኤል አደፍርስን የግላቸው ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከደደቢት ወጣት ቡድን የተገኘው አማካይ እስከ 2012 ድረስ በሰማያዊ ለባሾቹ ቤት ቆይቶ 2013 ወደ ሰበታ አቅንቶ ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር። ኃይለሚካኤል በበኩሉ የእግር ኳስ ህይወቱን ሰበታ ከተማ ብቻ ማከናወኑ ይታወቃል። ከሰበታ የተገኙት ሁለቱም ተጫዋቾች የሦስት ዓመት ውል መፈረማቸውም ተገልጿል።