መስፍን ታፈሰ ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማውን አኑሯል

ከሰዓታት በፊት መስፍን ታፈሰ እና ኢትዮጵያ ቡና ከስምምነት ደርሰዋል ብለን የሰራነው ዘገባ የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹም በይፋ ፈርማውን ማኖሩ ታውቋል።

በዝውውር ገበያው በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ቡናማዎቹ ወጣቱን አጥቂ መስፍን ታፈሰን ለማስፈረም መስማማታቸውን ከሰዓታት በፊት መዘገባችን ይታወቃል።

አሁን ክለቡ ይፋ ባደረገው መረጃ ፈጣኑ አጥቂ መስፍን ታፈሰ ለሁለት ዓመት ለቡናማዎቹ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል። የወጣቱ አጥቂ ወደ ክለቡ መቀላቀል አቡበከር ናስርን ላጣው የቡድን የማጥቃት አቅም ብርታት ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።

ኢትዮጵያ ቡና ኃይለሚካኤል አደፍርስ እና አብዱልአዚዝ ቶፊቅን እና መስፍን ታፈሰን ማስፈረሙ ሲረጋገጥ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል።