ኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ አስፈርሟል

የዝውውር ገበያው ከተከፈተ ጀምሮ ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመው ኢትዮጵያ ቡና ሰባተኛ ፈራሚውን አግኝቷል።

ለ2015 የውድድር ዘመን በአዲስ መልክ ቡድን እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች እስካሁን ስድስት ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ሲቀላቅሉ የአንድ ተጫዋችን ውል አራዝመዋል። በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋች እንደሚያስፈርሙ የሚጠበቁት ቡናማዎቹ አሁን ባገኘነው መረጃ የመሐል ተከላካዩ ወልደአማኑኤል ጌቱን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

በኢትዮ ኤሌትሪክ ከታችኛው ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በመጫወት የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ወልደአማኑኤል በያዝነው ዓመት ነበር ሰበታ ከተማን መቀላቀል የቻለው። በሰበታ መለያ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየው መሀል ተከላከያ በመጪው የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ቡና መለያ የምንመለከተው ይሆናል።