ድሬዳዋ ከተማ ከአሠልጣኙ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

የውድድር ዘመኑ አጋማሽ ላይ ድሬዳዋ ከተማን የተረከቡት አሰልጣኝ ሳምሶን ከቡድኑ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።

በዘንድሮ ዓመት አብዛኛውን የጨዋታ ሳምንት የወራጅነት ስጋት ኖሮበት በመጨረሻው ጨዋታ ባገኘው ነጥብ ለከርሞ በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን አስራ አምስት ሳምንታት ቡድኑን ሲያሰለጥኑ ከቆዩት አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር ለመለያየት መወሰኑን ሰምተናል።

አሰልጣኝ ሳምሶንን እንዳይቀጥሉ ያደረገው ድሬዳዋ በምትካቸው ሌላ አሰልጣኝ ለመቅጠር እያጤነ መሆኑንም አውቀናል። አሰልጣኙ ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት የሚቀራቸው ቢሆንም ተስማምተው መለያየታቸውን ከሁለቱም ወገን አረጋግጠናል።